About the Bureau

የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተልዕኮ፣ ርዕይ እና እሴቶች ተግባርና ሃላፊነት

ተልዕኮ

በክልሉ የሚገኙ ባህላዊ፣ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ሃብቶችን በመለየት፣ በማጥናት፣ በመጠበቅ፣ በማልማትና በማስተዋወቅ ለክልሉ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና አካባቢያዊ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸዉ ማድረግ፡፡

ርዕይ

የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ቀዳሚ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ልማት መሰረት ሆኖ 2022 ዓ.ም የክልሉን ዓመታዊ ምርት 20 በመቶ ሸፍኖ ማየት፡፡

እሴቶች

  • እንግዳ ተቀባይነት፣
  • ብዝሀነትን ማክበር፣
  • ለለውጥ እንተጋለን፣
  • የላቀ አገልግሎት፣
  • አሳታፊነት፣
  • ለህብረተሰብ ጥቅም ቅድሚያ እንሰጣለን፣
  • ግልጽነት፣
  • ተጠያቂነት፣

በቀጣይ 10 ዓመት በተቋሙ ትኩረት የሚደረግባቸው ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች

ባህል እና ቱሪዝም ዘርፍ በቀጣይ የ10 ዓመት ዕቅድ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት፣ባለፉት አመታት በአፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጥንካሬዎችን፣ድክመቶችን፣የመልካም አጋጣሚዎችንና ስጋቶች የግምገማ ውጤቶች፣ክልሉ ያለውን እምቅ አቅም እና ወቅቱ የሚጠይቀውን ነባራዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ የርብርብ ማእከል የሚሆኑ የሚከተሉት ትኩረት መስኮች ተለይተው ቀርበዋል፡፡

  1. የቅርስና መስህብ ሃብቶች ዘላቂ ጥበቃ እና እንክብካቤ፣
  2. የባህል እሴቶችና ኢንዱስትሪ ልማት፣
  3. የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማትና የላቀ ተወዳደሪነት፣
  4. የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ፣
  5. ተቋማዊ አቅም ግንባታ፣